ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ የሕክምና ባለሙያዎች ባነሡት ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም አብዛኛው ሐኪም ያነሣው ጥያቄ ተገቢነት እንዳለው ገልጸው፣ ጥያቄው በመምህራን፣ በሚዲያ እና ሌሎች የሥራ ዘርፎች የተሰማሩም ሁሉ የሚያነሡት መሆኑን ጠቁመዋል።
“ሚኒስትሩም፣ ፖሊሶችም፣ ወታደሮችም… ሁላችንም የደመወዝ ጥያቄ አለብን፤ ለጥያቄው በሰከነ እና አቅምን ባገናዘበ መልኩ ምላሽ እየሰጠን መሄድ ያስፈልጋል” ሲሉም አብራርተዋል።
አብዛኞቹ ሐኪሞች ያቀረቡትን ተገቢ ጥያቄ ለፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚያስቡ ሰዎች መኖራቸው እንደታየ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት።
“ፔሮል ላይ ፈርመው የማያውቁ ‘የደመወዝ ጭማሪ ይደረግ’ እያሉ ሲጮኹ ይሰማል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ጥያቄው በውይይት እና ስክነት እንጂ በጩኸት እንደማይመለስ ገልጸዋል።
“በጩኸት ከሆነ የጀመርናትን ጭላንጭል እናጠፋታለን እንጂ ውጤት አናመጣም” ሲሉም ተናግረዋል።
በጋራ ሆነን ሀገርን በማይጎዳ መንገድ መፍትሔ እያበጀን፣ ኢኮኖሚው እያደገ፣ ግሽበቱ የሚቀንስበትን መንገድ እንከተላለንም ነው ያሉት።
በፋሲካው ታደሰ
#EBC #EBCdotstream #PMAbiy #Ethiopia