በኢትዮጵያ ተጨማሪ 11 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

3 Yrs Ago
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 11 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 2424 የላቦራቶሪ ምርመራ 11 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 261 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ19-47 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ) ፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (መቐለ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 11

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 0

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 0
ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስድስት (106) ደርሷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top