አሜሪካ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አስታወቀች

6 Hrs Ago 57
አሜሪካ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አስታወቀች
አሜሪካ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አስታውቃለች።
ከ3 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ የዘለቀውን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወደ ዋይት ሀውስ እንደገባሁ በ24 ሰዓታት ውስጥ አስቆመዋለሁ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፤ ነገሮች እንዳሰቡት ቀላል የሆኑላቸው አይመስልም።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ወደ ሀገሪቱ የሚላክን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከልክለዉ እንደነበርም ይታወሳል።
አሁን ግን ኬቭ የግድ ራስዋን ለመከላከል የአሜሪካ ድጋፍ ስለሚያስፈልጋት ድጋፉ እንዲቀጥል መወሰናቸዉን አስታዉቀዋል።
በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ኬቭ የሚላከዉ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚያካትትም ተነግሯል።
የአሜሪካ ድጋፍ ይፋ የተደረገዉ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የሚሳዔል እና የሰዉ አልባ የጦር አዉሮፕላን ጥቃቷን አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ሲሆን፤ ድገፉን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ከሩሲያ በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩንም የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top