የገቢዎች ሚኒስቴር በሩብ አመቱ 193 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

8 Mons Ago
የገቢዎች ሚኒስቴር በሩብ አመቱ 193 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ከ193 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ሊሰበስብ ካቀደው 196.36 ቢሊዮን ብር ውስጥ 193.98 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98.78 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በ4 ወራት አፈፃጸም ከሀገር ውስጥ ገቢ 128.49 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 129.18 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 105 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ለመሰብሰብ ከታቀደው 67.88 ቢሊየን ብር ገቢ ውስጥ 64.79 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98.45 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ በመግለጫው አንስተዋል፡፡

አፈጻፀሙ ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 30.99 ቢሊዮን ወይም የ19.02 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ለተመዘገበው አፈፃጸም ውጤታማነትም በዋናነት በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች እየዳበረ የመጣው ጠንካራ የስራ ባህል መሆኑን መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡ 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top