በኢትዮጵያ እየተስፋፉ የሚገኙ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን እሴት በመጨመር ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚኖራቸው ጤማታ ጉልህ ነው።
ከዚህ ባለፈ ከውጪ በሚገቡ የምግብ እና የግብርና ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ረገድ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች አይነተኛ ጠቀሜታ አላቸው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የዱቄት ፋብሪካዎች፣ የምግብ ዘይት ማምረቻዎች፣ የእንስሳት ውጤት እና ማቀነባበሪያ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያዎች እንዲሁም ቡናን እሴት ጨምረው ለገበያ የሚያቀርቡ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ ይገኛል።
ይህም የሥራ ዕድልን ከመፍጠር ባለፈ እንደሀገር የምግብ ሉኣላዊነትን ለማረጋገጥ ያግዛል።
ይህን በተመለከተ የኢቢሲ አዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ እንግዶችን ጋብዞ አነጋግሯል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርክ ድጋፍ ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አያልነህ አባዋ፣ የአግሮ ኢንዱስትሪ ምርቶች በበርካታ የዓለም ሀገራት ተሞክሮ ውጤት ማስገኘታቸውንና ልምዱን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ በሥራ ላይ የሚገኙ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንደስትሪዎች የአርሶ አደሩ ምርት በግብዓትነት በመጠቀም ግብርናውን እና ኢንደስትሪውን እያስተሳሰሩ በመሆኑ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ብለዋል።
አርሶ አደሩን በቀጥታ ከምርት አቀነባባሪዎች ጋር ማገናኘት ያስቻለ አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመው፣ ይህም የገበያ ሰንሰለቱን በማሳጠር እና አርሶ አደሩን እና ኢንዱስትሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉንም አንስተዋል።
ለአብነትም በይርጋለም አካባቢ ለግብርና ማቀነባበሪያ ፋብሪከ ግብዓት የሚሆን የአቮካዶ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ በማቅረብ ገቢያቸውን ማሳደግ እንዲሁም ምርቱን በእጥፍ ማሳደግ እንደተቻለም ገልጸዋል።
የቲኬ ግሩፕ ማኒፋክቸሪንግ ኤንድ ትሬድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት እና ሥራ አስፈፃሚ ሼህ ቶፊቅ ከድር በበኩላቸው፣ በመንግሥት በኩል የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶችን አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል።

በመንግሥት ለኢንደስትሪ ፓርኮች መሠረተ ልማቶች ግንባታ መንሥት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አልሚዎች መሠረታዊ ግብቶችን ከተሟላላቸው በወናናት ማሽን መትከል እና ሥራውን ማስኬድ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት።
ይህም የልማት እንቅስቃሴውን ለማሳደግ እንደሚረዳ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራም አመቺ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪ መንግሥት በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከወጪ እና ገቢ ምርቶች ጋር በተያያዘ ያሉትን አሠራሮች ቀልጣፋ እና ቀላል በማድረጉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭን ማፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#EBC #EBCdotstream #Agro_industry #Agriculture