ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች

2 Mons Ago
ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኖርዌይ የአየር ንብረት ለውጥ የአከባቢው ሚኒስትር አንደርሰን ኤሪክሰን ናቸው።

ስምምነቱ እ.አ.አ እስከ 2027 ድረስ የሚቆይ ነዉ ተብሏል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በማጠናከር የአየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ እንደሚያገዝ ተጠቅሷል።

የዛሬው ስምምነት ኢትዮጵያ እየሰራች ያለዉ ዘላቂ የአረንጓዴ ደን ልማት ውጤታማ መሆኑን ማሳያ እንደሆነም ነዉ የተገለፀው።

ከካርበን ሽያጭ የሚገኘው ገቢ እንደ ሀገር የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ለማጠናከር አንዲሁም አዳዲስ የደን ልማት ስራዎችን ለመስራት ይውላል ተብሏል።

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top