ትምህርት ቤቶችን እያዘጋ ያለው በአውሮፓ ሀገራት የተከሰተው የሙቀት ማዕበል

15 Hrs Ago 87
ትምህርት ቤቶችን እያዘጋ ያለው በአውሮፓ ሀገራት የተከሰተው የሙቀት ማዕበል
በአውሮፓ ሀገራት የተከሰተውን ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች እየተዘጉ ነው።
 
እስካሁን ባለው መረጃ በጣሊያን ሁለት ሰዎች፣ በጀርመን ሁለት ሰዎች፣ እንዲሁም በስፔን ሁለት ሰዎች በሙቀቱ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
 
ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እንዲሁም ጣሊያን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
 
ሙቀቱን ተከትሎ ፈረንሳይ ትምህርት ቤቶችን የዘጋች ሲሆን የኤፍል ታወር አናቱ ለጎብኝዎች ዝግ እንዲሆን ተደርጓል፤ ጣሊያን ከትምህርት ቤት በተጨማሪ ከቤት ውጭ ሥራን ገድባለች።
 
በፖርቹጋል ከ46 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ፣ በስቴን ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንዲሁም በጀርመን ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ከፍተኛ ሙቀት መመዝገቡ ተጠቅሷል።
 
ሙቀቱን ተከትሎ በአውሮፓ ሀገራት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ እና ወደ ድንገተኛ የእንክብካቤ ማዕከላት የገቡ ሰዎች መኖራቸውን ዲ ደብሊው ዘግቧል።
 
የተመዘገበው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያልተለመደ እና ወደሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም እየተዛመተ መሆኑ ተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ኤጀንሲም ጥንቃቄ እንዲደረግ እያስጠነቀቀ ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top