የሶቬት ህብረት የመጨረሻው ፕሬዝዳንት ሚካይል ጎርባቼቭ በ91 ዓመታቸው አረፉ

1 Yr Ago
የሶቬት ህብረት የመጨረሻው ፕሬዝዳንት ሚካይል ጎርባቼቭ በ91 ዓመታቸው አረፉ
የቀድሞው ሶቬት ህብረት የመጨሻው ፕሬዝዳንት ሚካይል ጎርባቼቭ በ91 ዓመታቸው ማረፋቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል፡፡ ጎርቫቼቭ በከፍተኛ ህመም ሲሰቃዩ ቆይተው ትላንት አመሻሽ ማረፋቸው ነው የተገለጸው፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑን በሚካይል ጎርቫቼቭ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን መግለጻቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ የቀደሞዋ ሶቬት ህብረትን እ.አ.አ ከ1985-1991 የመሩት ሚካኤል ጎርባቼቭ በዓለም ሁለት ጎራ ተከፍሎ በነበረው 'ቀዝቃዛው ጦርነት' ምክንያት ሶቭየት ህብረት ከአሜሪካ የነበራትን ግንኙነት እንዲለዝብ ማድረግ ችለዋል ይባልላቸዋል። ጎርባቼቭ ስልጣን ላይ እንደወጡ የሶቬት ህብረት መልሶ ግንባታ (perestroika) እና በተለይ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ግልጽነት (glasnost) እንዲሰፍን በሚል ያስተዋወቋቸው ማሻሻያ አዘል ፖሊሲዎቻቸው ዝነኛ አድርጓቸዋል፡፡ ጎርባቼቭ ከአሜሪካ አቻቸው ሮናልድ ሬገን ጋር የኒውክለር መሣሪያ የመቀነስ ስምምነት ማድረጋቸውም በሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ታሪክ ይታወሳል። ዓለም ላይ ርዕዮተ ዓለም ተኮር ጭምር የሆነው ቀዝቃዛው ጦርነትን ተከትሎ የኒውከለር ጦር መሳሪያ ስጋትን በማስወገዳቸው የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ለመሆንም በቅተዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን ጎርቫቼቭ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ምዕራባዊያንን አምነው የፈጸሟቸው ስህተቶች በወቅቱ ለተፈጠረው ለሶቬት ህብረት ወድቀት የአገሬው ዜጋ ጭምር ተጠያቂ ያደርጓቸዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top