የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል ኢትዮጵያን በማጽናት ለትውልድ ያሻግራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

11 Mons Ago
የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል ኢትዮጵያን በማጽናት ለትውልድ ያሻግራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

 

የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት አስመርቋል።

ኮማንዶዎቹ የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልዕኮዎች ጠንካራ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።

በምርቃቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) “የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ስነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

ይህ ኃይል ውጊያ ማስቀረት እና ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ውጊያን የመጨረስ ተልዕኮ አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይህቺን ትልቅ አገር አጽንቶ ለትውልድ ያሻግራል” ብለዋል።




አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top