ለልደት ስጦታ የተበረከተ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ረዳትን መግደሉ ተሰማ

10 Mons Ago 2141
ለልደት ስጦታ የተበረከተ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ረዳትን መግደሉ ተሰማ

 

ለልደት ስጦታ የተበረከተ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ቫለሪ ዛሉዝኒ ረዳት መሞታቸው ተነግሯል። በቦንብ ፍንዳታው ከ39 ዓመቱ ሻለቃ ቻስትያኮቭ በተጨማሪ የ13 ዓመት ወንድ ልጃቸው ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው።

ፍንዳታው የሻለቃው ልጅ የቦንቡን ቀለበት ሲያሽከረክር የተመለከተ የቤቱ አገልጋይ ከእጁ ተቀብሎ ለማስቀመጥ ሲሞክር የተፈጠረ መሆኑን የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚንስቴር አመላክቷል።

ፍንዳታውን አሳዛኝ አደጋ ሲል የገለጸው ሚንስቴሩ የአደጋው መንስኤ በአግባቡ ተጣርቶ እስኪቀርብ ድረስ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቋል። 

ፖሊሰ ከአደጋው በኃላ በአካባቢው ተጨማሪ ሁለት የእጅ ቦንቦችን ማግኘቱን በመጠቆም የአደጋው መንስኤ ቸልተኝነት ነው ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top