በአንድ የባቡር ጉዞ ከ1.5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ

10 Mons Ago 1453
በአንድ የባቡር ጉዞ ከ1.5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ

የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች የገቢና ወጪ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ የባቡር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉ ተመላክቷል።

በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አዳማ የባቡር ጭነት ጣቢያ ተገኝተው የማዳበሪያ ስርጭት ሂደትን የተመለከቱት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የባቡር ጭነት የማጓጓዝ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ገልጸዋል።

በዚህም የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች የገቢና ወጪ ጭነቶችን ከጅቡቲ ወደብ በፍጥነት በማንሳትና ወደ ሀገር ውስጥ በማጓጓዝ ረገድ የባቡር አቅም ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ለ2016/2017 የምርት ዘመን የሚያገለግል የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ በስፋት እየገባ መሆኑን ጠቅሰው፤ ማዳበሪያው በፍጥነት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ባቡር ትልቁን ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

የአፈር ማዳበሪያን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ከግዢ ጀምሮ እስከ ማጓጓዝ ባለው ሂደት በመንግሥት በኩል ጠንካራ የቅንጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top