በመቐሌ ከተማ በ6 ቢሊዮን ብር ወጪ የብረታ-ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሊገነባ ነው

8 Mons Ago
በመቐሌ ከተማ በ6 ቢሊዮን ብር ወጪ የብረታ-ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሊገነባ ነው

በ6 ቢሊዮን ብር ወጪ በኢትዮጵያ እና ቻይና ባለሃብቶች ትብብር የብረታ-ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመቐሌ ከተማ ሊገነባ ነው።

በአስር ወራት ውስጥ የሚገነባው ይህ ኢንዱስትሪ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

በዚህ ወቅት የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የሌጀንድ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ሃላፈነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ አስፈጊው ድጋፍ ይደረግለታል ብለዋል።

ሌሎች በግልና በማህበር የተደራጁ ባለሃብቶችም የዚህን የልማት ፕሮጀክት አርአያ ተከትለው በማልማት  ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መልእክት አስተላልፈዋል።

የብረታብረት ማምረቻው 75 በመቶ በኢትዮጵያዊው ባለሃብት ኢንጅነር ያሬድ ተስፋይ የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ በቻይናዊው ባለሃብት ሚስተር ሊ ዮን መሸፈኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሳምሶም ገብረመድህን ገልጸዋል።

የሌጀንድ ብረታ ብረት ማምረቻ ኢንደስትሪ 6ሺህ ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ይተባረክ አመሃ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ  ለሌጀንድ ብረታብረት ኢንደስትሪ  አሁን ከተሰጠው የግንባታ ቦታ  ባለፈም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ   ለማድረግ ዝግጁ መሆኑ አረጋግጠዋል።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top