ኦስትሪያ በማዕድን እና በታዳሽ ሃይል ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ ገለፀች

8 Mons Ago
ኦስትሪያ በማዕድን እና በታዳሽ ሃይል ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ ገለፀች

ኦስትሪያ በማዕድን፣ በግብርና፣ በታዳሽ ሃይል እና በእንስሳት እርባታ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚያዊ እድሎች እና የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ቀጣናዊ ልማቶች ላይ ያተኮረ ነበር።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦስትሪያ ኤምባሲ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስቀጠል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በማዕድን፣ ታዳሽ ኃይል፣ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ገልጸዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top