የየመኑ ሁቲ የአሜሪካ የደረቅ ጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ፈጸመ

3 Mons Ago
የየመኑ ሁቲ የአሜሪካ የደረቅ ጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ፈጸመ

 

የአሜሪካ ማዕከላዊ አመራር የሁቲ ኃይሎች ጂብራልተር ንስር በተባለቸው ግዙፍ የአሜሪካ የደረቅ ጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ቢፈጽሙም ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጿል።

የመርከቧ ኦፕሬተር መርከቧ ከኤደን ባሕረ ሰላጤ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እየተጓዘች እያለ "ምንነታቸው ባልተለዩ ተተኳሾች" እንደተመታች እና በጭነት መያዣዋ ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ነገር ግን አንድም የመርከቧ ሠራተኛ እንዳልተጎዳ ተናግሯል።

አምብሬ የተባለው የብሪታኒያ የባሕር ደህንነት ኩባንያ እንዳለው በማርሻል ደሴቶች ባንዲራ የታጀበች፣ የአሜሪካ መርከብ በየመን የኤደን ወደብ አቅራቢያ በምትጓዝበት ወቅት በሚሳይል መመታቷል ገልጿል።

አምብሬ መርከቧ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት የሌለባት እንደሆነች ገልጾ፣ ጥቃቱ አሜሪካ በቅርቡ በሁቲ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን መገምገሙን ሬውተርስ ዘግቧል።   


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top