በኢትዮጵያ እና በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገው የብድር ስምምነት አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ

1 Mon Ago 317
በኢትዮጵያ እና በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገው የብድር ስምምነት  አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ

በኢትዮጵያ እና በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት  አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር እና በኢትዮጵየያ መካከል የተደረገውን የ አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አዋጅ በአንድ ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

የተደረገው የብድር ስምምነት ኢትዮጵያ የወሰደችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በምክር ቤት አባላት ተነስቷል።

በተለይ የተገኘውን ድጋፍና ብድር ለታለመላቸው አላማ እንዲውልና በአግባቡ ከተመራ ማሻሻያውን በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል ተብሏል።

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስተሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ መንግስት ብድሮችና ድጋፎችን ለማግኘት ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እና በከፍተኛ ጥረት የመጣ ነው ብለዋል።

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ ከሰጠው 500 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ የአንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለማድረግ በትናንትናው ዕለት ማፅደቁም ይታወሳል።

በሰሎሞን አበጋዘ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top