ባለፉት 6 ወራት ከ84 ሺህ በላይ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ

26 Days Ago 248
ባለፉት 6 ወራት ከ84 ሺህ በላይ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ

ባለፉት 6 ወራት በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ከ84 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዛሬው ዕለት 886 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 14ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሾቹ በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስከ አሁን ከ84 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top