5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭና ሆሳዕና ከተሞች በይፋ ጀመረ

1 Mon Ago 498
5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭና ሆሳዕና ከተሞች በይፋ ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ሆሳዕና ከተሞች የአምስተኛ ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ።

በአለም ላይ ፈጣን የሆነው የአምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ዲጂታል አገልግሎትን ዕውን በማድረግ እና ከተሞችን በማዘመን፤ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተጠቁሟል።

መርሃግብሩን ያስጀመሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ ኩባንያው ቴክኖሎጂን አሟጦ በመጠቀም እና ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል።

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጪን መቀነስ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በማቅረብ ለዜጎች ዲጂታል መፍትሔ መስጠት የመርሃግብሩ ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በፊት በአዲስአበባ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ እና ሐዋሳ የአምስተኛ ትውልድ (5G) ኔትዎርክ ማስጀመሩ ይታወሳል።

በአስረሳው ወገሼ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top