ከ18 እና ከ20 አመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

1 Day Ago 98
ከ18 እና ከ20 አመት  በታች  የአፍሪካ  አትሌቲክስ  ሻምፒዮና  ዛሬ ይጀመራል
በናይጄሪያ አቢዮላ ስፖርት ማዕከል በሚደረገው ውድድር በመክፈቻው ኢትዮጵያ የምትጠበቅባቸው ውድድሮች ይደረጋሉ፡፡
 
በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ከ20 አመት በታች ፍጻሜ አትሌት ንብረት ክንዴ በብቸኝነት ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል፡፡ የፍጻሜ ውድድሩ ምሽት 3 ሰዓት ከ25 ላይ ይጀምራል፡፡
 
የሴቶች ከ20 አመት በታች 3 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ምሽት 3 ሰዓት ከ10 ይደረጋል፡፡ ቤተልሄም ጥላሁን፣ ትርሀስ ገ/ሕይወት እና ውድነሽ አለሙ ለአሸናፊነት የሚፎካከሩ አትሌቶች ናቸው፡፡
 
በ1500 ሜትር የወንዶች ከ18 አመት በታች ፍጻሜ ደግሞ ሳሙኤል ገ/ሃዋርያ እና አብርሀም ገ/እግዚአብሔር ይሳተፋሉ፡፡ ውድድሩ ምሽት 1 ሰዓት ከ40 ይጀመራል፡፡
 
በተመሳሳይ ርቀት በሴቶች ከ18 አመት በታች ፍጻሜ ኤልሳቤት አማረ፣ ደስታ ታደሰ እና ቦንቱ ዳንኤል ተወዳዳሪ አትሌቶች ናቸው፡፡
 
በሁለቱም የእድሜ ዕርከን የሴቶች 100 ሜትር ማጣሪያ እና ከ18 አመት በታች ሁለቱም ጾታ የ400 ሜትር ማጣሪያዎች እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌደሬሽን አሳውቋል፡፡
 
በአንተነህ ሲሳይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top