በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ክልል አስተባባሪ አቶ ሙሉ ወልደስላሴ ገለፁ።
የ4ጂ የኔትወርክ አገልግሎት ከተጀመረባቸው የትግራይ ከተሞች መካከል መቐለ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ሽሬ እና ውቅሮ ከተሞች ይገኙበታል፡፡
የ4ጂ ኔትወርክ መጀመሩ በትግራይ ክልል ያለውን የዳታ ኔትዎርክ ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡
የ2ጂ እና 3ጂ ሲም ካርዶች ተጠቃሚዎች ወደ ቴሌኮም ማዕከላት በመሄድ ወደ 4ጂ ሲም ካርዶች በነፃ መቀየር እንደሚችሉም ኃላፊው መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡