ፀሐይ ዲስክ ላይ ያለው ትልቅ የክሮናል ቀዳዳ የጂኦማግኔቲክ ማዕበል የመገናኛ እና የሬዲዮ ስርጭት መቆራረጥ ሊያስከትል ይችላል

3 Mons Ago
ፀሐይ ዲስክ ላይ ያለው ትልቅ የክሮናል ቀዳዳ የጂኦማግኔቲክ ማዕበል የመገናኛ እና የሬዲዮ ስርጭት መቆራረጥ ሊያስከትል ይችላል

የናሳ የጠፈር አየር ሁኔታ ትንበያ ማዕከል (SWPC) ወደ ምድር ፊት ለፊት በሚታየው የፀሐይ ዲስክ ላይ ያለው ትልቅ የክሮናል ቀዳዳ የጂኦማግኔቲክ ማዕበል ሊያስከትል ይችላል ይህም ለመገናኛ እና የሬዲዮ ስርጭት መቆራረጥ ሊያስከትል እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

አሁን ባለው ሁኔታ የጂኦማግኔቲክ አመላካቾች በአነስተኛ ደረጃ ላይ ናቸው።ነገር ግን ይህ ክስተት ተለዋዋጭ በመሆኑ በሚቀጥሉት ቀናት ሊጨምር ይችላል።

የናሳው SWPC በ G2 ደረጃ ላይ ያለው የጂኦማግኔቲክ አለመረጋጋት (geomagentic disturbance) ወደ G3 ደረጃ(ከፍተኛ ጂኦማግኔቲክ መረበሽ)ሊያድግ እንደሚችል እና የምልከታው ስራ ያለማቋረጥ ክትትል እንዲደረግ አሳውቋል።

ይሁን እንጂ የፀሐይ ቅንጣቶች ፍሰት(solar proton flux)ጠቋሚዎች የኤችኤፍ ሬዲዮ ግኑኝነት መስተጓጎል ሊያስከትሉ በማይችሉበት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ናቸው።

ነገር ግን በሚታየው የፀሐይ ዲስክ ላይ ከ12 በላይ የፀሀይ ንቁ ቦታዎች (sunspots) ከቀላል እስከ ውስብስብ እና ያልተረጋጋ መግነጢሳዊ አወቃቀሮች የሚታዩበት ሰለሆነ ቀጣይነት ያለው ክትትል ያስፈልጋል።

በመሆኑም በተለያዩ ሶሻል ሚድያዎች ስለክስተቱ እየተላለፉ እንደሚገኘው የሬዲዮ ስርጭት ፤ የጂፒኤሰ እና ኢንተርኔት አገለግሎት መቋረጥን በተባለው ደረጃ የማያስከትል መሆኑን እስካሁን የተተነተኑ የጠፈር ትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ እንገልጻለን።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ሁኔታውን እየተከታተለ ወቅታዊ መረጃ እንደሚያደርስ እናሳውቃለን።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top