ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር ጉባኤ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ

16 Days Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር ጉባኤ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።
 
ጉባኤው ማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።
 
የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ አላማ ያነገበም መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ድጋፍ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም ዕድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top