የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን በዛሬው ዕለት የሚያከብሩ ሀገራት

13 ቀን በፊት
የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን በዛሬው ዕለት የሚያከብሩ ሀገራት

ትንሣኤ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሰው ልጆችን ለማዳን መስዋዕትነት የተከፈለበት ዕለት በመሆኑ በልዩ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው።

የዘመን አቆጣጠሯን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር በማናበብ የቀመረችው ኢትዮጵያ የ2016 የትንሣኤ በዓልን በዛሬው እለት በልዩ ሁኔታ እያከበረች ትገኛለች።

የጎርጎሮሳውያን ዘመን ቀመርን የሚከተሉ ካቶሊኮች እና ሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት ክርስቲያኖች ፋሲካን ቀድመው አክብረውታል፡፡

የኦሪዬንታል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ፣ አርመን፣ ሶሪያ እና የህንድ አብያተ ክርስቲያናት የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣዔ እያከበሩ ያሉት በዛሬው ዕለት ነው።

የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች የሆኑት ሩሲያ፣ ግሪክ፣ ጆርጂያ፣ ሰርቢያ፣ ቤላሩስ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ቡልጋሪያ፣ መቄዶኒያ እና ሞልዶቫም በዓሉን የሚያከብሩት በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት ነው፡፡

ከዓለማችን ህዝብ እስከ 300 ሚሊዮን ወይም 12 ከመቶው የሚሆነው ህዝብ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ግብጽ ከፍተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ናቸው።

በምስራቅ አውሮፓ የሚገኙት እንደ ሩሲያ፣ ግሪክ፣ ጆርጂያ፣ ቡልጋሪያ፣ መቄዶኒያ እና ሞንቴኔግሮ ከፍተኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡

በለሚ ታደሰ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top