በኮሪደር ልማቱ ተነሺ የሆኑ ዜጎችን ቅሬታ ተከታትሎ የሚፈታ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

10 Days Ago
በኮሪደር ልማቱ ተነሺ የሆኑ ዜጎችን ቅሬታ ተከታትሎ የሚፈታ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማቱ ተነሺ የሆኑ ዜጎችን ቅሬታ የሚሰማበት አሰራር፣ ቅሬታዎችን ተከታትሎ የሚፈታ እና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባዔው በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የ1 ወር ከ15 ቀን የአፈፃፀም ሪፖርት በከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀርቧል።

ከንቲባ አዳነች በሪፖርታቸው፤ በአምስቱ ኮሪደሮች እና በዓድዋ መታሰቢያ ዙሪያ ከቅደመ ዝግጅት አንስቶ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት የአሰራር ሂደትን አስቃኝተዋል።

በአሰራር ሂደቱ የተገኙ አዳዲስ የአሰራር ሂደቶች፣ የአመራሮች ሚና፣ የህዝቡ ቀናኢ ተሳትፎ እና የተቋማት ቅንጅት የሚደነቅ ነበር ብለዋል።

በኮሪደር ልማቱ ተነሺ የሆኑ ዜጎች ቅሬታ የሚሰማበት አሰራር እና ቅሬታዎችን ተከታትሎ የሚፈታ እና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ የሚመክር ይሆናል።

በሰለሞን ከበደ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top