ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነትን ማሳያ ነው፡-አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

16 Days Ago
ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነትን ማሳያ ነው፡-አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነትን ማሳያ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በኢትዮጵያ የሥራ ቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዡዩአንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አሰናብታዋል።
 
አምባሳደር ታዬ፤ ዣኦ ዡዩአን በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
 
በተለይም በሁለቱ ሀገራት ያለው ትብብር በወቅቶች የማይቀያየር ስትራቴጂያዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሱ ሀገራቱ የገነቡት ግንኙነት ልዩ፣ ጠንካራ እና አርዓያነት ያለው መሆኑን እንደሚያረጋጥ ተናግረዋል።
 
ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነት ሌላኛው ማሳያ መሆኑን በመግለጽ፤ ይህም የአምባሳደሩን በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ ልዩ እንደሚያደርገውም ገልፀዋል።
 
ከዚህ በተጨማሪም በአምባሳደሩ የስራ ቆይታ ወቅት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መጠናቀቃቸውን አምባሳደር ታዬ አስታውሰዋል።
 
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top