ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገላቸው ነው

15 ቀን በፊት
ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገላቸው ነው
ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።
 
በአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
"ባክ ቱ ዩር ኦሪጅንስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውጭ ለሚኖሩ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ በሦስት ዙሮች የሚካሄድ ነው።
 
በዚህም ከታህሳስ 20 እስከ ጥር 30 በመጀመሪያው ዙር "ከብዝኀ ባህል መሰረትዎ ጋር ይገናኙ" በሚል በተሰየመው መርሐ-ግብር ወደ ሀገራቸው ገብተው እንደነበር ይታወሳል።
 
አሁን ደግሞ "ታሪካዊ መሰረትዎን ይወቁ" በሚል በተሰየመው መርሐ-ግብር በሁለተኛ ዙር ወደ ሀገር እየገቡ ይገኛሉ።
 
በሁለተኛው ምዕራፍ ኢትዮጵያውያን የእረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው የሀገራቸውን ታሪክ እንዲያውቁ፣ የአያቶቻቸውንና ቅድመ አያቶቻቸውን አይበገሬነትና መስዋዕትነት እንዲሁም ከራሳቸው አልፎ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ያበረከቱትን አስተዋፅዖ አንዲረዱ በማድረግ የሀገር ፍቅር ስሜታቸው እንዲዳብር ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
 
በዚህ አኩሪ ታሪክ ተነሳስተው በዘመናቸው ፍሬያማ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱም ለማስቻል መሆኑ ተጠቅሷል።
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬት፣ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች የዋጋ ቅናሽ በማድረግ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያኑን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ ናቸው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top