አንድ የናይጄሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ወደተሳሳተ ከተማ በረራ ማድረጉ ታወቀ

8 Mons Ago
አንድ የናይጄሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ወደተሳሳተ ከተማ በረራ ማድረጉ ታወቀ

በተሳሳተ ከተማ ባረፈው አውሮፕላን ላይ የነበሩ አንድ ፖለቲከኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ አየር መንገዱ ለስህተቱ ተገቢውን ይቅርታ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን "እንደስድብ" ይቆጠራል ብለዋል።

የዩናይትድ ናይጄሪያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከዋናው ከተማ ሌጎስ በመነሳት የፌዴራል ዋና ከተማ በሆነችው አቡጃ ሊያርፍ ዕቅድ የነበረው ቢሆንም፣ ከ450 ኪሎ ሜትር በላይ ርቃ በምትገኘው አሳባ በተባለች ከተማ እንዳረፈ ዘገባው አመልክቷል።

ዩናይትድ ናይጄሪያ አየር መንገድ "በመዳረሻው ላይ በነበረው መጥፎ የአየር ሁኔታ" ምክንያት በረራው ወደ አሳባ እንደተዘዋወረ ገልጿል።

ነገር ግን ቢቢሲ ያናገራቸው ካንሶ ለተባለች ግዛት ሀገረ ገዢነት የሚወዳደሩት ሳሊሁ ታንኮ ያካሳይ የተባሉ አንድ ተሳፋሪ "ሰማዩ የጠራ ነበረ"፤ ነገር ግን አብራሪው ከሌጎስ "የተሳሳተ የበረራ ዕቅድ" ይዞ እንደተነሳ ተናግሯል ብለዋል።

አክለውም አብራሪው ይህንን ያስታወቀው የአውሮፕላኑ በሮች ከተከፈቱ በኋላ እንደሆነ እና አንዳንድ መንገደኞች በአቡጃ እንዳልነበሩ በማየታቸው "ተደናግጠው" እንደነበረ ተናግረዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top