እስራኤል በጋዛ ዳግም በጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ በሰዓታት ውስጥ 32 ፍልስጤማውያን ተገደሉ

7 Mons Ago
እስራኤል በጋዛ ዳግም በጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ በሰዓታት ውስጥ 32 ፍልስጤማውያን ተገደሉ

የእስራኤል ጦር በጋዛ ዳግም ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ በ3 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በፈጸመው የአየር ጥቃት 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ፡፡

በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ወታደራዊ ዘመቻ ዳግም መጀመሯን አስታውቃለች፡፡

የተኩስ አቁም ፋታው ማብቃቱን ተከትሎ እስራኤል በሰዓታት ውስጥ በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶች 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለሰባት ቀናት ከዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ አሁን ላይ በጋዛ የተከተለው ጥቃት ለብዙዎች አስደንጋጭ ሆኗል።

ሐማስ የስምምነቱ አካል የሆነውን በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዲገባ መፈቀድ ቢኖርበትም እስራኤል በመከልከሏ ስምምነቱን ጥሳለች ማለቱን ተጠቅሷል።

እስራኤል በበኩሏ ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ስምምነቱ ተጥሷል ብላለች።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ለተኩስ አቁሙ አለመራዘም ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ እየተካሰሱ ሲሆን ዳግም ስምምነት እንዲደረግ በግብጽና ኳታር በኩል ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top