ቦርስያ ዶርትመንድ ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ አለፈ

11 ቀን በፊት
ቦርስያ ዶርትመንድ ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ አለፈ

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ 2ኛ ዙር ጨዋታ ቦርሲያ ዶርትመንድ ፒኤስጂን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የቦርስያ ዶርትመንድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማትስ ሁሜልስ በግንባሩ ማስቆጠር  ችሏል።

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ቦርስያ ዶርትመንድ ፒኤስጂን በድምር ውጤት 2 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።

ቦርስያ ዶርትመንድ በ11 ዓመታት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎው ፒኤስጂን በድምር ውጤት 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ለፍፃሜ ማለፉን ያረጋገጠው።

የቦርሲያ አሰልጣኝ ኤደን ታርዚች ከድሉ በኋላ በሰጡት አስተያየት "ፓሪስ የመጣነው ብዙ ጠንካራ ጎኖች ያሉትን ቡድን ለመፋለም ነበር፤ በሰራነው ጠንካራ የቡድን ስራ መጠነኛ እድል ታክሎበት ጠፋጭ ድል አስመዝግበናል ብለዋል።

ድሉ ህልም የሚመስል እውነት ነው፤ ተጫዋቾችን፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን አንዲሁም ደጋፊዎች ሁሉንም ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።

የፒኤስጂ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በበኩላቸው፤ እግር ኳስ አንዳንዴ ኢ-ፍትሐዊ ነው፤ 31 ጊዜ ወደ ግብ ያደረግናቸውን ሙከራዎች ወደ ግብ መቀየር አልቻልንም ሲሉ ገልጸዋል።

በሁለቱም የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ያሳየነው ጨዋታ ዝቅተኛ የሚባል አይደለም፤ ከሁሉም በላይ ለፍፃሜ ባለማለፋችን ከልብ አዝነናል ብለዋል አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top