ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ5ኛው የተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ውጤታማ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይት አድርገዋል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

1 Yr Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ5ኛው የተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ውጤታማ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይት አድርገዋል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ5ኛው የተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ውጤታማ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደር መለስ ዓለም እንዳሉት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከነበርንበት የግጭት ዐውድ ወጥተን ወደ ኢኮኖሚ ግንባታ ተሸጋግረናል።
የቻይና፣ ኳታር፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና ሌሎች አገራት ባለሀብቶች መዋዕል ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ላይ በሚሰማሩበት ሁኔታ መክረዋል ብለዋል።
የኳታር ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማምረቻው እና በኮንስትራክሽን ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል።
ከሰባ በላይ የሚሆኑ የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት በአዲስ አበባ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የኢትዮ-ካናዳ የቢዝነስ ፎረም የካናዳ ባለሀብቶች በግብርና ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያሳዩበት መድረክ እንደነበርም ማስታወሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top