ለ40 ዓመታት በነፃ ሻይ ቡና ያቀርቡ የነበሩት የመዲናው ተወዳጅ ሼህ

13 Days Ago
ለ40 ዓመታት በነፃ ሻይ ቡና ያቀርቡ የነበሩት የመዲናው ተወዳጅ ሼህ
ሼህ ኢስማኢል አል-ዘይም አቡ አል-ሳባዕ በየዓመቱ ወደ መካ መዲና ለሚሄዱ ሀጃጆች ለ40 ዓመታት በነፃ ሻይ እና ቡና እያፈሉ ሲያቀርቡ የነበሩ ሰው እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። በእርግጥም ከእርሳቸው ሻይ እና ቡና የጠጣ ስለሼሁ ከዚህ በላይ ይላል።
 
ታዲያ አሁን እኚህ ሰው ይህን ለእርሳቸው የዕለት ተግባራቸው የሆነው ለብዙዎች በናፍቆት የሚጠጣው የበረከት ሻይ እና ቡና በፍቅር ሊታዩ ትዝታም ሊሆኑ ተገደዱ።
 
በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት እና መዲና ለሚመላለሱ እንደዘመድ የነበሩት እኚህ ቅን ሰው በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
 
ሼህ ኢስማኢል በሶሪያ ሀማ ከተማ ቢወለዱም፤ በመካ መዲና ግን ላልፉት 50 ዓመታት ኖረዋል። ታዲያ ከዚህ ውስጥ ብዙውን ዘመናቸውን ያሳለፉት ከዚህ በጎ ተግባራቸው ጋር ነው።
 
ሼህ ኢስማኢል ከተለያዩ ሀገራት ቅድስናን ሽተው ወደ መካ መዲና ለሚጎርፉ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ሀጃጆች ትኩስ ሻይ፣ ቡና እና ምግብ ያቀርቡ ነበር።
 
ታዲያ ማቅረባቸው አልነበረም አስደናቂው ነገር ለእነዛ ሁሉ ሰዎች ሻይና ቡናውን የሚያቀርቡት ካለምንም ክፍያ በነፃ መሆኑ እንጂ።
 
በመስጂድ እና በመዲና ቅዱሳን ቦታዎች ጭምር እንግዶችን በማስተናገድ አገልግሎት የሚታወቁም ሼህ ነበሩ።
 
ሼህ ኢስማኢል ሻይ ከማቅረብ ባለፈ፤ ከቅድመ አያቶቻቸው አካባቢ ባህላዊ የሆነ ጣፍጭ ምግብ ሲመጣላቸውም ለሀጃጆች በደስታ ያከፋፍሉ ነበር።
 
እኚህ በሀጃጆች ዘንድ የማይዘነጉ እና የሚወደዱት የመዲናው ሼህ ኢስማኤል በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
 
በናርዶስ አዳነ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top