ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ ድንበራቸው ላይ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶችን በአፋጣኝ ለመፍታት ተስማሙ

1 Yr Ago
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ ድንበራቸው ላይ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶችን በአፋጣኝ ለመፍታት ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ ድንበራቸው ላይ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶችን በአፋጣኝ ለመፍታት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
የኢትዮ-ኬንያ ድንበር ተሻጋሪ የደህንነት ምክክር በትላንትናው ዕለት በናይሮቢ መካሄዱን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በዚህም በፀጥታ እና ድንበር ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
በውይይቱ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልዑካን ቡድን ከኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በተለያዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የኬንያ ፕሪንሲፓል ሴክሬቴሪ ዶ/ር አብርሃም ኮሪር ሲንጎይ በድንበር አካባቢ ያሉ ስጋቶችን በጋራ ለመዋጋት የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን ነው አምባሳደር ባጫ ደበሌ የገለጹት።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top