ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር ተፈራረመች

4 Mons Ago 412
ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር ተፈራረመች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ታሪካዊ የሆነ የምግባቢያ ሰነድ ፈርመዋል።

የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሊላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሰነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖር ግንኙነታቸው ማዕቀፍ የሚሆን ነው።

ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባሕር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው።

እንዲሁም ሰነዱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የሚኖራቸው ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት ነው። ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርሕ እና ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመሥራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያፀና ነው።

ይህ ሰነድ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው ነው። እንዲሁም ሰነዱ ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ደኅንነት የሚገባትን ሚና እንድትጫወት የተሻለ ዕድል የሚፈጥር ነው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top