የፓስፖርት አመልካቾች ፓስፖርታቸው በሁለት ወራት ይወስዳሉ - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

1 Mon Ago
የፓስፖርት አመልካቾች ፓስፖርታቸው በሁለት ወራት ይወስዳሉ - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
የፓስፖርት አመልካቾች አዲስ በተጀመረው የዲጂታል አሰራር ፓስፖርታቸውን በሁለት ወራት እንደሚወስዱ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
 
አገልግሎቱ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ640 ሺህ በላይ ፓስፖርቶችን አትሞ ለደንበኞች ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፤ ከስድስት ወራት በፊት የተከማቸ የፓስፖርት ጥያቄን ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን አስታውሰዋል።
 
የአገልግሎቱ የህትመት ክፍል ቀን ከሌት በመስራት የፓስፖርት ህትመቱን በቀን ከ2 ሺህ ወደ 10 ሺህ ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
 
አሁን ላይ በፓስፖርት ስርጭት እና ህትመት ላይ የተጠራቀመ ፍላጎት ባለመኖሩ ዜጎች የፓስፖርት ጥያቄያቸውን በዲጂታል ስርዓቱ ካመለከቱበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ወራት ውስጥ መረከብ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡
 
ከብልሹ አሰራርና ሙስና ጋር ተያይዞ ከደላሎች ጋር ተመሳጥረው ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡
 
የአገልግሎት አሰጣጡን ከሰው ንክኪ ነፃ የሚያደርግ ጠንካራ የዲጂታል ስርዓት መዘርጋት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም ዳይሬክተሯ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top