ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር ነዳጅ መዝረፉን የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ

25/08/2022 09:17
ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር ነዳጅ መዝረፉን የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ
ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር /570 ሺ ሊትር / ነዳጅ መዝረፉን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአንቶኒዮ ጉተሬስ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ገልጸዋል፡፡ በቦታው የነበሩ የመንግስታ ድርጅት እርዳታ ሰጪዎች ዝርፊያውን ማስቆም እንዳልቻሉ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ የነዳጅ ክምችቱ ምግብ፣ መዳበሪያን እና አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚውል መሆኑም ተገልጿል፡፡ የነዳጁ በሕወሃት ቡድን መዘረፍ ለአከባቢው ማህበረሰብ የሚሰጠውን ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚጎዳው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰብዓዊ ስራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊያ አጥብቆ እንደሚያወግዝም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።
ግብረመልስ
Top