ኢትዮጵያ ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታወቀች

11 Mons Ago
ኢትዮጵያ ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታወቀች

ኢትዮጵያ ሦስተኛዋን ሳተላይት ወደ ሕዋ ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ መሆኗን የአገሪቱ ሕዋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር የሹሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደገለጹት ETRSS-2 ተብላ የምትጠራው ሦስተኛዋ ሳተላይት ከዚህ ቀደም እንደመጠቁት ሳተላይቶች ሁሉ የመሬት ምልከታ ታደርጋለች።

ሳተላይቷ ከሌሎቹ የተሻለ የምስል ጥራት እንደምትልክም ይጠበቃል ብለዋል - ኃላፊው።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ETRSS-1 እና ET-Smart-RSS የተሰኙ ሳተላይቶችን ማምጠቋ የሚታወስ ነው።

ከሦስት ዓመት በፊት የመጠቀችው ሳተላይት በሕዋ ላይ የመቆየት እድሜዋ 2 ዓመት ተኩል ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጠች እንደሆነ የገለጹት ም/ዳይሬክተሩ፣ ሁለተኛዋ ሳተላይት ግን በ6 ወሯ ገደማ እድሜዋን ጨርሳ አልፋለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነችውን ETRSS-01 ሳተላይት ከቻይና የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ሕዋ የላከችው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር።

ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ እና ለመልከዓ ምድር ጥናት የመረጃ አገልግሎትን እስካሁን ድረስ እየሰጠች ትገኛለች።

ሳተላይቷ በቻይና መንግሥት የተገነባች ሲሆን፣ በግንባታው ሂደትም በርካታ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ከቻይና አጋሮቻቸው ጎን ተሰልፈው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን የሹሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ምክትል ዳይሬክተሩ ሦስተኛዋ ሳተላይት ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ከመግለፅ ባሻገር ዝርዝር መረጃን አልሰጡም።

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ ሳተላይት ከቻይና በልገሳ በተገኘ 6 ሚሊዮን ዶላር እንደተገናባች እና በአጠቃላይ 210 ሚሊየን እንደፈጀች በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

ምክትል ዳይሬክተሩ የሹሩን (ዶ/ር)፣ ሦስተኛውን ሳተላይት ለማምጠቅ ያስፈለገበት ምክንያት እድሜዋንም ተሻግራ እስካሁን አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለችውን ሳተላይት ለመተካት መሆኑን አመልክተዋል።

ይህንንም ዕቅድ ለማሳካት የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት መካሄዱን እና ለግንባተው የሚያስፈለግው ዝግጅትም እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ እስከ ሦስት ዓመት ያህል ጊዜ ይወስዳል ያሉት ም/ዳይሬክተሩ፣ ከሦስት ዓመት በኋላ የተሻለ የምስል ጥራት ትልካለች የተባለችውን ET-Smart-RSS ሳተላይት ለማምጠቅ ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።  

ከዚህ ቀደም የመጠቁ ሳተላይቶች የሕዳሴው ግድብ ውሃ ሳይሞላ አንስቶ እስካሁን ያለውን ምስል መላክን ጨምሮ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለግብርና እና ለከተሞች ልማት እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት ሥራ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ምስሎችን መላካቸውን እና ውጤታማ መሆናቸውን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ከማምጠቋ በፊት እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ አገሮች በመግዛት ትጠቀም እንደነበር ባለሙያዎች ያስታውሳሉ።

በዚህም ሳቢያ የሳተላይት መረጃውን ለመግዛትም በዓመት 250 ሚሊየን ብር ስታወጣ የቆየች ሲሆን ይህም ከዓመት ዓመት ይጨምር እንደነበር የዘርፉ ባለሙያዎች ከዓመታት በፊት የተሰራ ጥናትን በመጥቀስ ይናገራሉ።

አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገራት በሕዋ ጥናት ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያ እና ግብፅ ጥሩ ስም መገንባት የቻሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን ከእነርሱ አንጻር ጀማሪ ናት።

መሬት

 

ሳተላይት የሙሰጠው ጥቅም?

የሕዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ስከሚኖርባት ምድር ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ካለው ፍላጎት ባሻገር ሕዋን አበጥሮ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።

ለዚህ ደግሞ ሳተላይቶች ዋነኛ መሳሪያዎቹ ናቸው። ከህዋ ላይ በመሆን መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል።

እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደኅንነትን ለመጠበቅ እና ለሌላም ይውላል።

የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት በዚህ ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት የበርካቶችን ሕይወት ለመታደግ ያስችላል።

ለአብነትም በአንድ አካባቢ ያሉ የዛፎችን ቁጥር፣ የአየርንብረት ለውጥ እና ሌሎች መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ የሚቻልበት ዕድል አለ።

ግብርናቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት የቱ አካባቢ ምርታማ ነው? የአየር ንብረት ለውጥ ሊኖር ይችላል? የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ ለመመለስ የሳተላይት መረጃ አስተማማኝ ና አስፈላጊ ነው።

አንድንየግብርና አካባቢን የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሃው፣ ስለ አፈሩ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት እናየሚገኘውን የምርትመጠን በትክክል ማወቅም ይቻላል።

በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችሲስገፋፉ ፋብሪካዎችየት መገንባት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ ከሳተላይትየሚገኙ መረጃዎችእጅግ ጠቃሚ በመሆን ያግዛሉ።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top