በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት ያጠናቀቁት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን አሸኛኘት ተደረገላቸው

1 Yr Ago
በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት ያጠናቀቁት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን አሸኛኘት ተደረገላቸው
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የነበራቸውን የአንድ ቀን ጉብኝት አጠናቀቁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸውም በተለያዩ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስማማታቸው ተነግሯል።
በንብረቴ ተሆነ

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top