ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል።
ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በተያያዘ ዜና ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።
