ፓራጓይ ከልቦለዳዊ ሀገር ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ባለስልጣኗን አባረረች

9 Mons Ago 347
ፓራጓይ ከልቦለዳዊ ሀገር ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ባለስልጣኗን አባረረች

የደቡብ አሜሪካዊቷ ፓራጓይ የግብርና ሚንስትር የሆኑት ኦርናልዶ ቻሞሮ ከተፈጥሮ በላይ ሃይል አለን በሚሉ ቡድኖች እንደተመሰረተች ከሚነገርላት "ዩናትድ ስቴትስ ኦፍ ካይላስ" ተወካዮች ጋር ባደረጉት የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ነው የተባረሩት::

ይህች ምናባዊት ሀገር “ከአለም ዙሪያ በተፈናቀሉ ሂንዱዎች እያንሰራራ ያለው የጥንታዊው የሂንዱ ስልጣኔ መነቃቃት” ናት በሚል ነው መስራቾቹ እንድትታወቅ ያደረጉት።

የፓራጓይ ባለስልጣናት የፆታ ጥቃትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች በህንድ የሚፈለጉት እራሳቸውን “አምላክ” ብለው በሚጠሩ ኒትያናንድ ተከታዮች ሲታለሉ የመጀመሪያዎቹ አይደሉም።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በኒውዮርክ፣ ኒው ጀርሲ የሚገኙ የአካባቢው ባለስልጣናት ከዚህች ምናባዊት ሀገር ጋር “የእህትማማችነት ከተማ” ስምምነትን ለመፈራረም ከጫፍ ደርሰው ነበር::

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ሊፈራረሙ የነበሩት ከንቲባው ለዚህ “አሳዛኝ ክስተት” ላሉት ተግባር ይቅርታ ጠይቀዋል።

ቻሞሮ ከአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የልብ ወለድ አገር ተወካዮች ከእርሳቸው እና የግብርና ሚኒስትር ካርሎስ ጊሜኔዝ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ተናገረዋል።

በቃለ መጠይቁ ወቅት ቻሞሮ ካይላሳ የተባለችው የልቦለድ ሀገር የት እንደምትገኝ እንኳን እንደማያውቁ በመግለጽ ይልቁንም ፓራጓይን በመስኖ ዘርፍ ለመርዳት ላቀረቡላቸው ድጋፍ የመግባቢያ ስምምነቱ ላይ መፈረማቸውን ተናገረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የካይላሳ ተወካዮች በየካቲት ወር በጄኔቫ በተደረጉ ሁለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባዎች ላይ መሳተፋቸውም ነው የተገለፀው፤ መረጃው የገልፍ ኒውስ ነው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top