አምቡላንስ ከማሽከርከር እና አሳ ከማስገር እስከ ስኬታማ ግብ ማደን

5 Hrs Ago 84
አምቡላንስ ከማሽከርከር እና አሳ ከማስገር እስከ ስኬታማ ግብ ማደን
በ2012 የ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ቼልሲ እና ኒውካስትል ዩናይትድ በየሮፓ ሊግ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ለማግኝት ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ተገናኝተዋል፡፡
 
ሊጉ ሊጠናቀቅ 4 ጨዋታዎች የቀሩበት በመሆኑ አሸናፊው ቡድን ዕድሉን የሚያሰፋበት ነው፡፡
 
ቼልሲ ካለው ስብስብ አንጻር እና ጨዋታውን የሚያደርገው በሜዳው መሆኑ የአሸነፊነት ቅድሚያ ግምቱን አግኝቷል፡፡
 
ቢሆንም በአሰልጣኝ አለን ፓርዲዮ የሚሰለጥነው ኒውካስትል ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ 2 ለ 0 አሸንፎ ተመለሰ፡፡
 
ኒውካስትል ከቼልሲ በአንድ ነጥብ ከፍ ብሎ የውድድር አመቱን ከማጠናቀቁ ባሻገር በዩሮፓ ሊግ መሳተፉን አረጋገጠ፡፡
 
በዚህ ወሳኝ ጨዋታ ሁለቱንም ግቦች ያስቆጠረው ተጫዋች ፓፒስ ዴምባ ሲሴ ነው፡፡
 
በተለይ በጨዋታው ያስቆጠራት አንደኛዋ ግብ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከተቆጠሩ የምንጊዜም ምርጥ ግቦች ከቀዳሚዎቹ ሆና ተመዝግባለች፡፡
 
የተወለደው በሴኔጋል ሴዲሁ ሲሆን ተጫዋች እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡
 
እግር ኳስ ከድህነት ማምለጫ መንገድ ከሆናቸው አፍሪካውያን አንደኛው እሱ ነው፡፡ ገና በ15 አመቱ የአምቡላንስ አሽከርካሪ ሆኖ ሰርቷል፡፡
 
ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኝው ፓፒስ ዴምባ ሲሴ ህይዎትን ለማሸነፍ በአንድ በኩል ዱዋንስ ለተባለ ቡድን እግር ኳስ ሲጫዎት በሌላ በኩል ደግሞ ህመምተኞችን በማመላለስ አገልግሏል፡፡
 
በአንድ አሮጌ አምቡላንስ ውስጥ ህመምተኞች እና በወሊድ ምክንያት ህይታቸው የሚልፍ እናቶችን በተደጋጋሚ ይመለከት የነበረው ሲሴ የአካባቢውን ሰዎች ከዚህ ችግር ለማውጣት ያልሞከረው ነገር የለም፡፡
 
የተወለደባት ሴዲሁ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት በመሆኑ በቂ ገንዘብ ለማግኝት ከአምቡላንስ አሽከርካሪነት ባሻገር በአቅራቢያው ከሚገኘው ካሳማስ በተባለ ሀይቅ ውስጥም አሳ አጥማጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡
 
አሳ በመሸጠ እና ከአምቡላንስ በሚያገኝው ገዘንዘብ ቤተሰቦቹን ይረዳ የነበረው ያኔው ታዳጊ ጎን ለጎን ያስኬደው የነበረው እግር ኳስ በመጨረሻም ህይወቱን የሚቀይርበትን አጋጣሚ ፈጠረለት፡፡
 
የስራው ጥንካሬ በእግር ኳሱም ይገለጥ የነበረው ፓፒስ ዴምባ ሲሴ የፈረንሳዩን ክለብ ሜትዝ ተቀላቀለ፡፡
 
አውሮፓን ከረገጠ በኋላ ነገሮች የቀለሉት አሳ እጥማጁ አጥቂ ኒውካስትል ዩናይትድ ራሱን ለአለም በሚገባ ያስተወወቀበት ክለብ ነው፡፡
 
ፍራይበርግ ፌነርባቼ እና ሌሎችም የተጫወተባቸው ክለቦች ሲሆኑ ሲሴ የተወለደበትን አካባቢ ለመርዳት በየአመቱ ለ15 ቀን በሴኔጋል ያሳልፋል፡፡
 
ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ተቋማትን መርዳት ሁልጊዜም በድብቅ የሚያደርገው ስራው ሆኖ ቀጥሏል፡፡ 1 ሜትር ከ80 የሚረዝመው አጥቂ ባለፈው አመት ራሱን ከእግር ኳስ ማግለሉን ካሳወቀ በኋላ ዳግም ተመልሶ በዱባይ እየተጫወተም ይገኛል፡፡
 
በአንተነህ ሲሳይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top