የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ተጀመረ

3 Mons Ago
የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ተጀመረ
የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት በአገር ውስጥ ክትባቶችን በማምረት በቀጣናው ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚችልና ተስፋ የተጣለበት መሆኑ ተገልጿል።
 
ግንባታው በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን፤ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
 
ዶክተር ሊያ በዚሁ ወቅት፥ የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት ታስቦ ነሐሴ 24 ቀን 2014 በሚኒስትሮች ምክር ቤት መቋቋሙን ገልጸዋል።
 
ይህ የመንግስት የልማት ድርጅት ኢትዮጵያ በክትባት ማምረት ዘርፍ የነበራትን ነባር እውቀቶች በማዋሃድ በአዲስ መልክ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።
 
የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት በ2027 የክትባት ንጥረ-ነገሮችን የማምረት ተግባር እንዲጀምር ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።
 
ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ድጋፍ ያደረጉትን የዓለም ባንክ፣ የዓለም የጤና ድርጅት፣ ሲዲሲ-አፍሪካ እና ሌሎች ተቋማትን አመስግነዋል።
 
በመርሃ ግብሩ ላይ በዓለም የጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ፣ የሲዲሲ-አፍሪካ ተወካይ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
 
በቶክ ሯች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top