ምክር ቤቱ የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ

1 Mon Ago 246
ምክር ቤቱ የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ18ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እንደገና ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
 
ሰብሳቢዋ ረቂቅ አዋጁ ነጻና ገለልተኛ የሆነ እና አደረጃጀቱ ከተጽዕኖ የጸዳ የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት በማቋቋም ጠንካራ የዳኝነትና የፍትህ ተቋማት ለመፍጠር የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ተጠሪነት ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማዕከል ያደረገ ጥናትና ምርምር በማድረግ የዳኝነትና የፍትህ ስርዓቱ ማዘመን እንዲሁም ህጎችን ከወቅታዊ የዓለም እና የሀገሪቱ የዕድገት ደረጃ ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ ጠንካራ የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ አክለው አብራርተዋል፡፡
 
የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ እንደገና መቋቋሙ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ታአማኒና ቀልጠፋ አገልግሎት ለመስጠት ያሚያስችሉ የህግ ሙያተኞች ለማፍራት እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡
 
ቀድመ ስልጠና የሚለው በስራ ላይ ሂደት የፍትህ ባለሙያዎችን እያበቁ መሄድ ቢቻል፣ በየቦታው የስልጠና መዕከል ከመክፈት ይልቅ በማዕከል በማድረግ ዘርፉን መደገፍ ቢቻል የሚል አስተያየት የምክር ቤት አባላት ሰጥተዋል፡፡
 
ከቅድመ ስልጠና ጋር በተያያዘ የፍትህ ባለሙያዎች ዳኞች እና ዐቃቢያን ህጎች በሰዎች ንብረት እና ህይወት ላይ ለሚወስኑት ውሳኔ በእውቅትና እና በክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የቅድመ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ አስረድተዋል፡፡
 
ኢንስቲትዩቱ በህግ ጉዳዮች ጥናት እና ምርምር በማድረግ እና ፖሊሲዎችን በማመንጨት እንደሀገር በፍትህ ሥርዓቱ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማረም እንደሚያግዝ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ አስረድተዋል፡፡
 
ኢንስቲትዩት ለፍትህ ሚኒስቴር ከነበረበት ተጠሪነት ወጥቶ፤ በአሁኑ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ መሆኑን በረቂቅ አዋጁ ተመላክቷል፡፡
 
ምክር ቤቱ የፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1369/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን የምክርቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top