የኪንታሮት ህመም (ሄሞሮይድስ)

3 Mons Ago
የኪንታሮት ህመም (ሄሞሮይድስ)

የኪንታሮት ህመም የታችኛዉ የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካባቢ ያሉ የደም መልስ (veins) የደምኪንታሮት ለበሽታው በትክክል ገላጭ ስም ባይሆንም፤ የኪንታሮት በሽታ በፊንጢጣ እና በታችኛው የአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም መላሽ ስሮች መላላትና መለጠጥ እንዲሁም በደም በመወጠር ማበጥ የሚከሰት ነው፡፡

ኪንታሮት በአንጀት ታችኛው ክፍል ሲፈጠር የውስጥ ኪንታሮት ሲባል በፊንጢጣ ላይ ከሆነ ደግሞ የውጪ ኪንታሮት ይባላል፡፡

በእድሜ ዘመን ከአራት አዋቂዎች ሶስቱ (75 በመቶ) የኪንታሮት በሽታ ሊያዛቸው ይችላል።

ኪንታሮት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖረው ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የሚታወቅ አይደለም፡፡

ብዙ ውጤታማ የህክምና ዘዴዎች እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለበሽታው መፍትሔ የሚሆኑ ናቸው ፡፡

የኪንታሮት ህመም ቧንቧዎች በሚያብጡበትና በሚቆጡበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት መሆኑን የህክምና ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡

የኪንታሮት ህመም ሰገራ በሚወጣበት ወቅት ሲማጥ፣ ወይም በፊንጥጣና በታችኛዉ የትልቁ አንጀት አካበቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ እንደ እርግዝናና ሌሎች ጭነትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት ሊከሰት ይችላል፡፡

ከእድሜ ጋር የኪንታሮት ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡ ምክንያቱም ከእድሜ ጋር ተያይዞ በፊንጢጣ እና በታኛው የአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም ስሮች ይደክማሉ፡፡

በእርግዝናም ወቅት የፅንሱ ክብደት በፊንጢጣ አካባቢ የሚኖረውን ግፊት ስለሚጨምረው ተመሳሳይ ለውጦች ይኖራሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

• ፊንጢጣ አካባቢ መብላት
• ህመም ወይም አለመመቸት
• ፊንጢጣ አካባቢ እብጠት
• ደም የቀላቀለ ሰገራ
• ኪንታሮቱ በፊንጢጣ በኩል ከወጣ ህመም እና መቆጣት ይኖራል
• ደም የቋጠረ የውጭ ኪንታሮት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠት፣ መቆጣት እና ፊንጢጣ አካባቢ እባጭ ሊያመጣ ይችላል፡፡
• የሰገራ ማምለጥ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳ ለኪንታሮት ዋነኛ ምልክቱ በሚፀዳዱበት ወቅት የደም መፍሰስ ቢሆንም በፊንጥጣ ደም መምጣት ሁሌ ከኪንታሮት ጋር ብቻ የተያዘ ሳይሆን እንደ የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የፊንጥጣ ካንሰር ምልክትም ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

የኪንታሮት መንስኤ ምክንያቶች፦

• በሚፀዳዱበት ወቅት ለረጅም ጊዜ ማማጥ
• መፀዳጃ ላይ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ
• ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ረዘም ላለ ጊዜ መኖር
• ውፍረት መኖር
• እርግዝና
• የፋይበር መጠናቸዉ አነስተኛ ወይም ፋይበር የሌላቸዉን ምግቦች ማዘዉተር ናቸዉ፡፡

ህክምናውን ስንመለከት

• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ
• የበኪም የተሚቀቡ መድሀኒቶችን መጠቀም
• ለብ ያለ ውሀ ላይ ትንሽ ጨው በማድረግ ፊንጢጣ አካናኒ ማጠን
• ህመም ማስታገሻ መውሰድ
• ቀዶ ህክምና የመሳሰሉ ህክምናዎች ናቸዉ፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top