በቀጣይ የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ፈጣን እና ንቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ

3 Mons Ago
በቀጣይ የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ፈጣን እና ንቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ

በቀጣይ የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ቁጥብ እና ተከታይ ሳይሆን ፈጣን እና ንቁ መሆን እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መመሪያ ሰጡ።

ለአስራ አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አመታዊ የአምባሳደሮች ስብሰባም ተጠናቋል፡፡

ይህንን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም እንዳሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር መለስ አለም እንዳሉት አቶ ደመቀ አድማሱና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወን እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት።

በቀጣይ የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ተደራሽነት፣ ተደማጭነት እና ተፈላጊነትን መጨመርን ግብ ማድረግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት።

ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚደረጉ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንዳለበትና ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ከሀገራት ጋር የሚኖረው ግንኙነትም የጋራ ጥቅምን ታሳቢ ያደረገ፣ በመከባበር ላይ የተመሰረተና በሽርክና ሊሆን እንደሚገባም ነው የተገለፀው።

የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴውም ቁጥብ እና ተከታይ ሳይሆን ፈጣን እና ንቁ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።

በቀጣይ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የውጭ ግንኙነት ስራ አስኳል ሆኖ እንደሚቀጥልም ነው የተገለፀው።

በወንደሰን አፈወርቅ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top