37 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

3 Mons Ago
37 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2016 በጀት መት የመጀመሪያው ስድስት ወራት ባከናወነው አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ፤ 37 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ፡፡
 
አገልግሎቱ በስድስቱ ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 45 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ፤ 37 የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ነው ገለጸው፡፡
 
ተቋሙ በያዘው ዕቅድ ከተሞቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት ማድረጉን ገልጾ፤ ነገርግን በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት እንዳልቻለ ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top