የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎበኙ

3 Mons Ago
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎበኙ

"አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ህብረ ቀለም" በሚል መሪ ሀሳብ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት በሚሊኒየም አዳራሽ የተዘጋጀው የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው እለትም በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ኤክስፖውን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ መርሀ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የአርብቶ አደር አካባቢዎች የያዙትን ዘርፈ ብዙ ፀጋ አውጥቶ መጠቀም እንዲቻል እና ለብልፅግና ጉዞ ተጨማሪ አቅም መፍጠር እንዲችሉ ፓርቲው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የአርብቶ አደር አካባቢዎች በብቸኝነት ከሚታወቁበት የእንስሳት ሀብት በተጨማሪ በግብርና፣ በመስኖ ልማት እንዲሁም በማዕድን ተጠቃሚ የሚሆኑበት እድሎችን ለመፍጠር ሰፋፊ ስራዎች መሰራተቸው ተገልጿል።

አመራሩ ያለበትን የመሪነት ሀላፊነት መሬት ላይ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም፣ የአርብቶ አደሩን ተፈጥሯዊ የአንቅስቃሴ ባህሪ ሊመጥን የሚችል አቅጣጫ በማሳየት ተጠቃሚነቱን ማስፋት ተገቢ እንደሆነ መገለፁን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top