300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

1 Mon Ago
300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
 
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸው ተጠቅሷል።
 
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መረጃዎችን ለኩባንያው አመራሮች አቅርበዋል።
 
ኢንቨስትመንቱ እንዲሳካ ኮርፖሬሽኑ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርግም አቶ አክሊሉ አረጋግጠውላቸዋል።
 
ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ እ.አ.አ በ2011 የተቋቋመና ተቀማጭነቱን በቻይና ያደረገ ኩባንያ ስለመሆኑ ተገልጿል።
 
እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ፣ በጋና፣ በናይጄሪያ፣ በኢራን እንዲሁም በአዘርባጃን በፋይበር፣ በሴራሚክ፣ በአልሙኒየም እና በሌሎች የምርት አይነቶች ተሰማርቶ የሚገኝ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑም ተጠቅሷል።
 
የኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸውም ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
 
በፓርኩ ለባለሀብቶች የሚቀርቡ የመብራት፤ ውሀ እና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶች ክፍያ ከሌሎች ተመሳሳይ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን እና ይህም ለኢንቨስትመንት ውሳኔያቸው ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top