በቀጣዩ የመኸር ምርት ዘመን የተሻለ የግብርና ውጤት እንዲገኝ ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ወደ ስራ እንዲገቡ አቶ አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ

1 Mon Ago
በቀጣዩ የመኸር ምርት ዘመን የተሻለ የግብርና ውጤት እንዲገኝ ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ወደ ስራ እንዲገቡ አቶ አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ
በቀጣዩ የ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን የተሻለ የግብርና ውጤት እንዲገኝ፤ አርሶ አደሮች፣ የግብርና አመራሮች እንዲሁም የግብርና አጋዥ አጋር አካላት ከወዲሁ ወደ ስራ እንዲገቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ከግብርና ዘርፍ አመራሮች እና ከግብርና አጋዥ አካላት ጋር በተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡
 
የክልሉ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ የግብዓት እና የማሽነሪ አቅርቦት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በተለይ አርሶ አደሩ የግብርና ማሽነሪዎችን በመጠቀም ውጤታማነቱ እንዲሻሻል ባለፉት ዓመታት የትራክተር አቅርቦት ላይ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
 
በዚህም ከ164 በላይ ትራክተሮች መሰራጨታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የቀረቡን ትራክተሮች በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
 
የሌማት ትሩፋት፣ የስንዴ ልማት እና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አቶ አሻድሊ ሀሰን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ከሊፋ በበኩላቸው፤ ባለፈው የ2015/16 የምርት ዘመን 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር በመሸፈን 32 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
 
በቀጣዩ የምርት ዘመንም የተሻለ ምርት ለማግኘት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ግብዓት አቅርቦት በአርሶ አደሩ እና በዘርፉ አመራሮች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቶ ባበክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በጀማል አህመድ
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top