የደብረብርሃን ከተማ ሰላምን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወን ችሏል፡- የከተማ አስተዳደሩ

1 Mon Ago
የደብረብርሃን ከተማ ሰላምን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወን ችሏል፡- የከተማ አስተዳደሩ
የደብረብርሃን ከተማ ሰላምን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ።
 
ባለፉት 8 ወራት በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት የከተማዋን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በታሰበው መልኩ እንዳይከናወን ማስተጓጎሉን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ተናግረዋል።
 
ታጣቂ ቡድኑ በፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በከተማዋ የሸቀጦች የዋጋ ንረት እንዲባባስ አድርጓል ብለዋል።
 
ከተማዋ የምትታወቅበት የኢንቨስትመንት ፍሰት ግስጋሴ እንዲገታ ስለማድረጉም ተቀዳሚው ምክትል ከንቲባ አንስተዋል።
 
ይሁንና የከተማ አስተዳደሩ ሰላምን ከማስጠበቅ ስራ ባለፈ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።
 
በ8 ወራት ውስጥ በተጠበቀው ልክ ባይሆንም 19 ኢንደስትሪዎች ወደ ማምረት ገብተዋል ብለዋል።
 
ነዋሪዎች ጥያቄ የሚያነሱበትን የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የመሬት አገልግሎትን ዲጂታል ማድረግ ስለመቻሉም ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት አንስተዋል።
 
አሁን ላይ የከተማዋ ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ፤ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን ለማከናወን መታቀዱንም አንስተዋል።
 
በዘላቂነት ሰላም እንዲመጣም ውይይትን ማስቀደም፣ የፀጥታ ኃይሉን ማጠናከር እና ህብረተሰቡ የሰላም ዘብ እንዲሆን የማድረግ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
 
በከተማዋ የተሻለ የልማትና የመልካም አስተዳደሮችን ለማከናወን ነዋሪው የሰላሙ ዘብ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
 
በሙሉ ግርማይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top