ባለፉት 8 ወራት መንግስት በኮንትሮባንድ ሊያጣ የነበረውን ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

13 Days Ago
ባለፉት 8 ወራት መንግስት በኮንትሮባንድ ሊያጣ የነበረውን ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

ባለፉት 8 ወራት መንግስት በኮንትሮባንድ ሊያጣ የነበረውን 10.5 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ኮንትሮባንድን መከላከል የተሰኘ ዳይሬክቶሬት አቋቁሞ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር ኮሚሽኑ እራሱን በሰው ሃይል በማደራጀት በሦስት ፈረቃ እየሰራ መሆኑንም የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡

ኬላ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞችን ከፖሊስ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ማሰልጠን መጀመራቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ይህም ለቁጥጥሩ ውጤታማነት የላቀ አስተዋፆ በማበርከት ላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኮሚሽኑ የቁጥጥር ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ማዘመን የሚያስችል ስርዓት ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት እያዘረጋ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡ 

ኮንትሮባንድ የሃገርን ኢኮኖሚ የሚያቀጭጭ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድርጊቱን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንዲሰሩም አቶ ዘሪሁን አሰፋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአፎሚያ ክበበው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top