እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለፀ

12 Days Ago
እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለፀ

እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ብልጫ አለው ተብሏል።

በባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ላይ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የተቻለው 5 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ እንደነበር የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ የግብርናው ዘርፍ የዘጠኝ ወራት አፈፃፅምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ የግዥ ሂደት ቀድሞ በመጀመሩ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

በዚህም ለበጋ መስኖ እና ለበልግ የሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ቀደም ብሎ መሰራጨቱን ገልፀዋል።

አሁን ላይ ደግሞ ወደ መኸር ዝግጅት እየተገባ በመሆኑ ክልሎች የደረሳቸውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ከወዲሁ ማሰራጨት እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

ለ2016/17 የምርት ዘመን23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ 19.4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ መፈፅሙም ተጠቁሟል።

በይመር አደም


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top